የካቲት 14 እና 15 ቀን 2017 በሞሮኮ በተካሄደው የ2024 የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ አመራር ሽልማት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ “Special African Business Leadership Award 2024” አሸናፊ በመሆን ሽልማታቸውን ተቀብለዋል ::

” African Business Leadership Award” ኮርፖሬት ተቋማትን በልዩነት የመሩና የአፍሪካ የንግድ ገጽታን በመቀየር የላቀ ስኬቶችን ያስመዘገቡ መሪዎች የሚሸለሙበትን ዘርፍ ነው አቶ ጀማል አህመድ በአህጉር ደረጃ ያሸነፉት!!!

አቶ ጀማል ከበርካታ የአህጉሪቱ ተወዳዳሪዎች መካከል ለአሸናፊነት የበቁት በእርሳቸው አመራር ኢትዮጵያ ዘላቂ እድገት እንድታስመዘግብ፣ ለበርካቶች የስራ እድል እንዲፈጠር ምክንያት በመሆን፣ ድርጅታቸው በመሠረተ ልማት ግንባታና በማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ግንባር ቀደም ተዋናይ እንዲሆን በማስቻል ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በመረዳትና በሃገር ሁለንተናዊ እድገት ላይ ያመጡትን ተጨባጭ ውጤት በመገንዘብ ነው።



ለመላ የድርጅታችን ሰራተኞችና ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንኳን ደስ አለን።







