የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ አካል የሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ የቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የተቀናጀ አመራር ስርዓት (Integrated Management System) በመተግበር ሰርተፍኬቶችን አገኘ።

ድርጅቱ በአራት ዘርፎች ማለትም በጥራት ሥራ አመራር (ISO 9001:2015)፣ በምግብ ደህንነት አመራር ስርዓት (ISO 22000:2018)፣ በሙያ ጤንነትና ደህንነት አመራር ስርዓት (ISO 45001:2018) እና የአካባቢ ጥበቃ ሥራ አመራር ስርዓትን (ISO 14001:2015) ተግባራዊ ማድረግ ችሏል።

ሰርተፍኬቱን የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ነፃነት ጋሻዬ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ተቀብለዋል።

አቶ ነፃነት ጋሻዬ ድርጅቱ የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረጉ የተሻለ ጥራት እና ደህንነቱ የተጠበቀ ምርትን ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልìዋል።

የአሰራር ስርዓቶቹ ቀጣይነት ያለዉ ክትትል ስለሚፈልጉ የድርጅቱ ሰራተኞች ስርዓቱን ለማስቀጠል በትጋት መስራት እንዳለባቸውም አሳሰበዋል።

የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ የሚድሮክ ድርጅቶች አለም አቀፍ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ደህንነታቸዉ የተጠበቁ ምርትና አገልግሎቶችን ለሀገር ዉስጥና ለዉጪ ገበያ በማቅረቡና እየሰራ ባለው ስራ የድርጅቱን አመራሮች አመስግነዋል።

ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ የቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ከ12 በላይ የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን በተሳካ ሁኔታ እየተገበረ ሲሆን የቡና ክምችት፣ ቡና ዝግጅት፣ የተቆላና ተቆልቶ የተፈጨ ቡና፣ የቡና ገለባ ከሰል ምርት፣ የቡና ጆንያ ምርት እና ሌሎች የአገልግሎት ስራዎችን ያከናውናል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ደረጃ የካይዘን አመራር ሥርዓትን ተግብረው ለውጥ ከማምጣት አንፃር የተሻለ ውጤት ካስመዘገቡ ድርጅቶች ጋር በመወዳደር ተሸላሚ እንደሆነ ይታወቃል።

ሚድሮክ ለሀገር -ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY