የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገ ውድድር ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር 7 ዋንጫዎች ተሸለሙ!

የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ አካል የሆነው በበቃ ቡና እርሻ የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ሲሆን
የኢትዮ-አግሪ ሴፍት 3 እርሻዎችም በተለያየ ደረጃ ተሸልመዋል።
ሽልማቱንም ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እጅ ዛሬ ተቀብለዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ


ኢትዮጵያ የዓለም የስራ ድርጅት (ILO) አባል የሆነችበት መቶኛ ዓመት መታሰቢያ ክብረ በዓልና ብሔራዊ የአሰሪና ሰራተኛ ጉባዔ
“ማህበራዊ ምክክርና የላቀ ምርታማነት
ለማህበራዊ ፍትህ!”


በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ሃይሌ ግራንድ ሆቴል ላለፉት 3 ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል።
ዛሬ በመርሀ-ግብሩ መዝጊያ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተገመገሙ ከ300 በላይ ድርጅቶች 30 ለሚሆኑት የዋንጫ ሽልማት የተሰጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሰባቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ወስዷል።
ሽልማቱ በተለያዩ ዘርፎች የመንግስት የልማት ድርጅቶችና የግል ድርጅቶች በሚል ተሰጥቷል።
በዚህም መሰረት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የወሰዳቸው ሽልማቶች፦
በግብርና ዘርፍ

 1. የሆራይዘን ፕላንቴሽንስ አካል የሆነው በበቃ ቡና እርሻ የወርቅ ደረጃ
 2. የኢትዮ-አግሪ ሴፍት አካል የሆነው ሆለታ አበባ እርሻ የብር ደረጃ
 3. የኢትዮ-አግሪ ሴፍት አካል የሆነው አየሁ እርሻ ልማት የብር ደረጃ
 4. የኢትዮ-አግሪ ሴፍት አካል የሆነው ውሽውሽ ሻይ ልማት የነሀስ ደረጃ
  በኢንዱስትሪ ዘርፍ
 5. ሆራይዘን አዲስ ጎማ የብር ደረጃ
 6. ብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን የነሀስ ደረጃ
  በአገልግሎት ዘርፍ
 7. ብሉ ናይል ሪዞርት ሆቴል የነሀስ ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል።
  ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቅርቡ 18 ድርጅቶቹ በታማኝ ግብር ከፋይነት፥ 9 ድርጅቶቹ ደግሞ በጥራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ መሆናቸው ይታወሳል።
  ይህን ሽልማት ለየት የሚያደርገው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የምርት ጥራት ለማምጣትም ይሁን ግብርን በታማኝነት ለመክፈል የሚያስችለውን ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር መቻሉን የሚያረጋግጥ መሆኑ ነው።
  ይህ ደግሞ ለአስተማማኝ የምርት ጥራትም ሆነ ግዴታን ለመወጣት መሰረታዊ ነገር በመሆኑ ሚድሮክ ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተሸላሚዎቹና ሃላፊዎቹ አረጋግጠዋል።
  የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀ-መንበር ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ የዘወትር ፍላጎትና ራዕይ በአዲሱ አወቃቀርና በአቶ ጀማል አህመድ ዋና ስራ አስፈጻሚነት በሚመራው ተቋማዊ አደረጃጀት አመርቂ ውጤት ማምጣቱን ያሳየ ውጤት ነው ብለዋል ተሸላሚዎቹ።
  ሃላፊዎቹ አክለውም ለክቡር ሊቀ-መንበበራችን፥ ለዋና ስራ አስፈጻሚያችን፥ ለምክትል የዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች፥ አመራሮችና በተለይም ለውጤቱ መምጣት ቀጥተኛ ባለድርሻ ለሆኑት ሰራተኞች በሙሉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

 • RMOHA SOFT Drinks Industry
 • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY