የሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ በኢንተግሬትድ ማኔጅመንት ሲስተም ማለትም በኳሊቲ ማኔጅመንት ሲስተም (ISO 9001-2015)፣ ኢንቫይሮንመንታል ማኔጅመንት ሲስተም (ISO 14001-2015 ) እና ኦኮፔሽናል ሄልዝ ኤንድ ሴፍቲ ማኔጅመንት ሲስተም (ISO 45001-2018) ሰርተፍኬት አግኝቷል።
ሁዳ ሪል እስቴት ደግሞ በኳሊቲ ማኔጅመንት ሲስተም (ISO 9001-2015) ሰርተፍኬት አግኝቷል ፡፡
ሰርተፍኬቶቹን የኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፍ ም/ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ኃ/ ማርያም፣ የሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ በርሄ እና የሁዳ ሪል እስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉጌታ ተፈራ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ እጅ ተቀብለዋል።
የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ የሚድሮክ ድርጅቶች አለም አቀፍ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ደህንነታቸዉ የተጠበቁ ምርትና አገልግሎቶችን ለገበያ ለማቅረብ እየሰሩት ላለው ስራ የድርጅቱን አመራሮች አመስግነዋል።
የአሰራር ስርዓቶቹ ቀጣይነት ያለዉ ክትትል ስለሚፈልጉ የድርጅቱ ሰራተኞች ስርዓቱን ለማስቀጠል በትጋት መስራት እንዳለባቸውም አሳሰበዋል።









