የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፣ ባለፈው የ12ኛው ዙር የጥራት ሽልማት መርሃ-ግብር ላይ ካሉት 20 ድርጅቶች 14ቱ መሸለማቸው ይታወሳል።
ዘርፉ ያገኘውን ስኬት ወደ ተቀሩት ኩባንያዎች ለማሸጋገር እንዲቻል፤ በምርት ጥራትና አመራር፣ በሰው ሀብት አስተዳደር እንዲሁም በደንበኛ እርካታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሶስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ ለሚገኙ ሰራተኞችና አመራሮች ተሰጥቷል።
ስልጠናው በኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ድርጅት በቅርቡ የተሻሻሉ የጥራት መስፈርቶችን ተከትሎ የተሰጠ ሲሆን፤ የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ መከናወን ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።
የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ድርጅት የጥራት መስፈርቶቹን በየጊዜው በማሻሻል፣ የኢትዮጵያ ምርቶችና አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ደረጃን አሟልተው እንዲመረቱና ተወዳዳሪነታቸው እንዲጨምር በማድረግ ላይ ይገኛል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድርጅቶችም የጥራት መስፈርቶቻቸውን በየጊዜው በማሻሻል፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለገበያ ለማቅረብና የደንበኛን እርካታ ማዕከል ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ።
ይህ ስልጠና ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ድርጅት በተለያዩ ደረጃዎች ሽልማት የተቀበሉ ድርጅቶች ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገሩና በቅርቡ ዘርፉን የተቀላቀሉ ኩባንያዎች ደግሞ መስፈርቶቹን አሟልተው ተሸላሚ መሆን እንዲችሉ የሚያግዝ ነው።
ስልጠናው በቀጣይነት በሌሎች የምርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴዎች ላይ አተኩሮ ለተቀሩት ድርጅቶችና ሰራተኞችም የሚሰጥ ይሆናል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድርጅቶች በ12ኛው ዙር የጥራት ሽልማት መርሃ-ግብር ላይ 28 ሽልማቶችን ማግኘታቸው ይታወሳል።










