የሞሐ ምርቶችን ያለ ምንም መቆራረጥ ለህብረተሰቡ ለማድረስ ወሳኝ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ።ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አዲሱን የፔፕሲ ሎጎ አስተዋውቋል ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በቅርቡ የተቀላቀለው ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ተወዳጅ ምርቶቹን በመያዝ በድጋሚ ወደ ገበያ በስፋት መግባቱን አስመልክቶ በአዘጋጀው ፕርግራም ላይ አዲሱን የፔፕሲ ሎጎ አስተዋውቋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አሰፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ሞሐ ገጥሞት የነበረውን የአመራርና ተያያዥ ችግር ቀርፎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል።

ተቋማዊ መዋቅርን መሰረት ካደረጉ ውስጣዊ ማሻሻያዎች ጎን ለጎን ከፔፕሲኮ ጋር በመተባበር የተሰሩ ስራዎችም ውጤታማ እንደነበሩ አቶ ጀማል አስረድተዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እንደ አዲስ ከመደራጀቱ በፊት ብዙ ድረጅቶች ኪሳራ ሲያስተናግዱ እንደነበር ያስታወሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው አሁን ላይ ግን ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ ዉጤታማ ከመሆን ባለፈ ለወገን ደራሽ መሆናቸውንም ጭምር ተናግረዋል።

የድርጅቱ ምርቶች ያለ ምንም መቆራረጥ ለሚወዳቸው ህብረተሰብ ለማድረስ ወሳኝ ስራዎች መሰራታቸውንም አቶ ጀማል አስረድተዋል።

የሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ሙሄ በቡኩላቸው ሞሐ ትርፋማ በመሆን ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣትም ጭምር ለህዝብ አለኝታነቱን ያረጋግጣል ብለዋል።

ቀደም ብሎ በፔፕሲኮ የተዋወቀው አዲሱ የፔፕሲ ሎጎ በመድረኩ ላይ ለእንግዶች ይፋ ተደርጓል።

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ 8 ፋብሪካዎች ያለው ሲሆን ምርቶቹም ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ አፕል፣ ሚሪንዳ ኦሬንጅ፣ ሚሪንዳ ቶኒክ እና 7 ኣፕ ናቸው።

Recent News

Archives

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY