ማዕከሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀማል አሕመድ በጋራ መርቀዋል::
ከንቲባ አዳነች ሚድሮክ የሣር ቤት ፕላዛ ሞልን ዉብና ማራኪ አድርጎ በራሱ ቦታና በራሱ ሀብት ሰርቶ ለአገልግሎት ክፍት በማድረጉ ለህዝቡ ያለዉን አክብሮት ማሳየቱን ገልጸዋል።
ሚድሮክ ከዚህ በፊትም ከአምባሳደር እስከ እስጢፋኖስ ድረስ ያለዉን የወንዝ ዳር ልማት በራሱ ወጪ በመስራትና በተለያዩ መንገዶች ድጋፎችን በማድረጉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብልዋል።
ኑ የነገዋን አዲስ አበባ ዛሬ እናስጎብኛችሁ!
ይህ የትናንት ሳይሆን የነገ ሀውልታችን ነው፡፡ ልክ እንዳባቶቻችን ጊዜን የመቅደማችን፤ ሥራን የመውደዳችን ጠቢብ የመሆናችን ምልክት፡፡
እኛው በእኛው ሀብት የምንሰራው፤ የመቻላችን ሰንደቅ፡፡
እዚህ መንደር ትናንት አለ፡፡ የጥንቷ አዲስ አበባ ትውስታ ከጎጆ ቤቶቿ ይቀዳል፡፡ ከዘመን ብንርቅ እንኳን ስማቸው የሰፈር መጠሪያ ሆኗል-ሣር ቤት፡፡
ደግሞም ነገን የናፈቁ መሪዎች ስለ አፍሪካ ነፃነትና አንድነት ድርጅት የመሰረቱት ከዚሁ ሳይርቁ ነበር፡፡
የኋላችን ምልክቷ የነጋችን መስታወቷ ሣር ቤት ዛሬም ከታሪክ ሰሪዎቹ ጋር አብራለች፡፡ ሚድሮክ ኢንቨስመንት ግሩፕ እንደ መሪ ቃሉ ሁሉ ስለ አገር አስቦ በወርቃማ ብዕሩ በዚች መንደር የነገ ትዝታችንን እየፃፈ ይገኛል፡፡
ቦታው የታሪክ ጥለት ሆኖ መሀመዲያ ቪሌጅ እየተሰራበት ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክት በከታማችን ውስጥ ያለ ሌላ ውብ ከተማ ነው፡፡ 250 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው መሐመዲያ ቪሌጅ በርግጥም የአዲስ አበባ አዲስ መልክ ሊሆን ተቃርቧል፡፡
ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን ሆቴል ፣47 ቅንጡ የመኖሪያ ቪላዎች፣74 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ ግዙፍ ሞል፣13 ሺህ ካሬ የሚሸፍኑ የንግድ ሱቆች እና 1500 አፓርታማዎች ሁሉም በአንድ ላይ በመሐመዲያ ቪሌጅ፡፡
ይህ ሕልም አይደለም፤ እውነት እንጂ፡፡ ለዛውም ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያ የሚሰጡት ድንቅ ገጸ በረከት፡፡ ትናንት ቅንጡውን ሸራተን አዲስ ሆቴል በመዲናችን ገንብቶ የማይደበዝዝ አሻራን ያኖረው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እንደ አገሩ ልማድ ሁሉ አንድ ያጣላል ብሎ ሌላኛውን ቅንጡ ፎር ፖይትንስ ባይ ሸራተን ሆቴልን ሣር ቤት ላይ እየገነባ ይገኛል፡፡
በርግጥም አሁን አራት ዓመት ስንት ነው? ብንል ያምርብናል፡፡
አዎ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አራት ዓመት ወይንም 1460 ቀናት ስጡኝ እኔ ደግሞ ቅንጡ ከተማ እሰጣችኋለሁ ብሏል፡፡
መሀመዲያ ቪሌጅ የሚል ስም የወጣለት በከተማችን ውስጥ የሚገነባው ይህ ቅንጡ ከተማ ከፍ ብለን ከጠቀስናቸው የሆቴል፣የመኖሪያ መንደር የንግድ ሱቅና መሰል አገልግሎቶች በተጨማሪ 8 ሺህ መኪኖችን በአንዴ ማቆም የሚያስችል ፓርኪንግ፣ዘመናዊ ሬስቶራንቶች፣የልጆችና ወጣቶች መዝናኛ እንዲሁም የሕዝብ መናፈሻ ይኖረዋል፡፡
ይህ ቃል አይደለም፡፡ በፍጥነት ለመታየት ለመዳሰስ የበቃ ለውቧ መዲና የቀረበ ስጦታ እንጂ፡፡ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት ጥቂት ገጸ-በረቶችን እነሆ ብሏል፡፡
ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ የተሰራው የውሃ ፋውንቴን የመሀመድያ ልዩ በረከት የከተማችን ደምቀት ሆኗል፡፡
አሁን ሣር ቤት የትናንት ትዝታችን ብቻ አይደለችም፡፡ ዛሬን ቀድመን ነገ ላይ የቆምንባት ፌርማታ እንጂ፡፡ እነዛ መታወሻ ጎጆ ቤቶቿም የሽያጭ ቢሮ ሆነው ወደ ነገ የሚያደርሱ አሳንሰር ሆነዋል፡፡
ይህም ብቻ አይደለም ድካም ቢሰማዎ አረፍ የሚሉበት ቢያሻዎት ደግሞ ዘና የሚሉበት የእናንተው ሸራተን አዲስ በሳር ቤቷ ልዩ ሬስቶራንት ከፍቶ ይጠብቃችኋል፡፡
በከተማ ውስጥ ሌላ ከተማ – መሀመዲያ
ይምጡና የነገዋን አዲስ አበባ ዛሬ ይጎብኙ፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የሀገር ሀብት!











