ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፉ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ታደሰና ሌሎች አመራሮች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ፀጋ የታደለች ሀገር መሆኗን አንስተዋል።
ሀገሪቱ በተፈጥሮ የተሰጣትን የቡና ፀጋ በአግባቡ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንድትሆን እየሰራችው ያለውን ስራ በማገዝ ረገድ ስታርባክስ ሁሌም ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
የቡናን ምርትና ምርታማነት በምርምር በመደገፍ ኩባንያቸው ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠውል።
በአለምአቀፍ ደረጃ እያጋጠመ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥና በቡና ዘርፍ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ችግር በመፍታት ረገድ ስታርባክስ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በጋራ ይሰራል ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንቱ።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቡናው ዘርፍ እየሰራ ያለውን ስራ ያደነቁት ምክትል ፕሬዚደንቱ ሮቤርቶ ቬጋ አሎንሶ ስታርባክስ ከግሩፑ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናከሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የስታርባክስ ምክትል ፕሬዚዳንት በጉመርና ኮሳ የቡና እርሻ ማሳዎች በተመለከቱት ነገር መደሰታቸውን ገልፀዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ለሀገር የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት በተለያዩ ጊዜያት ሽልማቶችን የወሰደ የሀገር ሀብት ተቋም ነው፡፡










