የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ጥራት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ለጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገለፁ።

ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴና የኢትዮጵያ የጥራት ድርጅት የቦርድ አመራሮች በሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ላይ በተደጋጋሚ የ1ኛ ደረጃ የልህቀት ዋንጫ ተሸላሚ የሆነው ሆራይዘን አዲስ ጎማን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

የጉብኝቱ አላማም የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት አለም አቀፍ የልህቀት ሞዴልን መሠረት አድርጎ ባዘጋጀው የጥራት ሽልማት ውድድር ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ለተከታታይ አመታት በማሸነፉ ተሞክሮዎቹን ለሌሎች ተቋማት ለማጋራት ያለመ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የጥራት ድርጅት የበላይ ጠባቂ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ታየ አጽቀሥላሴ ከጉብኝቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ለጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን በተግባር ያረጋገጥንበት ጉብኝት ነው ብለዋል።

ክቡር ፕሬዚዳንቱ ባደረጉት ንግግር ጎማ ለአንድ ሀገር እስትራቴጅክ ምርት መሆኑን ጠቅሰው ሆራይዘን አዲስ ጎማ ጥራት ያላቸውን የተለያዩ ጎማዎችን በማምረት ለገበያ በማቅረብ የሀገረ ኩራት መሆኑን ገልጸዋል።

እዉቀት ከማሸጋገር እና የዉጪ ምንዛሬን ከመተካት አንጻርም ከፍተኛ ሚና እየተወጣ በመሆኑም አመስግነዋል።

የምርት አይነቶቹን በማስፋት ጊዜው የሚፈልጋቸውን የአሰራር ስራርዓት በመከተል እየሰራ መሆኑን በመግለፅ በጥቂት ጊዚያት ዉስጥ ምርቶቹን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የሃገር ኩራት እንደሚሆን ተሰፋ እንዳለቸውም ተናገረዋል።

ሆራይዘን እየሠራ ያለው ሥራ ለሌሎች አምራች ኢንዳስትሪዎች አርዓያ የሚሆን ድርጅት በመሆኑ ለጥራት ትኩረት በመስጠት የምትሰሩትን ሥራ አጠናክራችሁ መቀጠል ይኖርባችኋልም ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ የድርጅቱን ባለቤትና ሊቀመንበር ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ይህን የሀገር ኩራት የሆነና መሰል በርካታ ተቋማትንም ስላበረከቱ፣ ከልባቸው ሀገራቸውን ስለሚዱ እና የዜጎቻችንን ኑሮ ለማሻሻል ስለሚያደርጉት ከፍተኛ ጥረት አመስግነዋል፡፡

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY