የድል ቀን -ሚድሮክ ለሀገር -ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ሆራይዘን አዲስ ጎማ በ12ተኛው ዙር የጥራት ሽልማት ልዩ የልህቀት ተሸላሚ ሆነ።

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ይህንን ልዩ ሽልማት ያገኘው በጥራት ሽልማት ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ አንደኛ በመሆን በማሸነፉ ነው።

ተቋሙ በጥራት ልዩ የልህቀት እና በአንደኛ ደረጃ የልህቀት ዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል ።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ከኢፌዴሪ ፕሬዚደንት እና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ታዬ አጽቀሥላሴ እጅ ሽልማቱን ተቀብለዋል።

በ12ኛው ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ፕሮግራም ላይ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድርጅቶች 28 ሽልማቶችን አግኝተዋል ።

ኩባንያዎች የጥራት ሽልማቶችን በልዩ የልህቀት፣ በአንደኛ ደረጃ የልህቀት፣ በ2ኛ ደረጃ የልህቀት፣ 3ኛ ደረጃ የልህቀት፣ በከፍተኛ አድናቆት፣ በአድናቆትና በተሳትፎ ደረጃዎች ተሸልመዋል። 

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ሚድሮክ  ለደንበኞቹ ጥራት ያላቸውን ምርትና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ሁሌም ተግቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

ድርጅቱ የተለያዩ የምርትና አግልግሎት ስራዎች ላይ በመሰማራት ከ79 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር፣ የዉጪ ምንዛሬን በማስገባት፣ ተኪ ምርቶች በማምረት እና ከፍተኛ ግብር በመክፈል የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በማሳደግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ እንደሚሰራ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።

ሚድሮክ ለሀገር-ሚድሮክ ኢንቨስትመንት

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY