ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቤንች ሼኮ ዞን የተገነባው ደንቢ ኢኮ ሎጅ ጠ/ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል።
ኢኮ ሎጁ የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ባለፉት ሰባት አመታት ዘላቂነትን፣ የቅርስ ኃብትን እና ለዘመናት የሚዘልቅ አለምአቀፍ ደረጃን የመጠበቅ እድል መፍጠርን በማዋሃድ ምን ያህል እንደተለወጠ ማሳያ ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ (ዶ/ር) ናቸው።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ሎጁ የሀገር በቀል ኢኮኖሚክ ማሻሻያው ባመጣው ዉጤት መሰረት በሀገር ዉስጥ በከፍተኛ ጥራት የተመረቱ ምርቶችን በመጠቀም ጥንካሬና ዘመናዊነትን በተላበሰ መልኩ ከአከባቢው የተፈጥሮ ሀብት ጋር እንዲስማማ ታስቦ የተሰራ ነው ብለዋል ።
በአፍሪካ ግዙፉ የቡና እርሻ በሆነው በበቃ የቡና እርሻ ልማት አጠገብ የተሰራዉ ይህ ሎጅ የክልሉን እና የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ የሚያሳድግ እንደሆነ ተናግረዋል ።
ደንቢ ኢኮ ሎጅ ቱሪስቶች የማይረሳ ጊዜን እንዲያሳልፉ በከፍተኛ ጥራት በሚድሮክ ፡ኢንቨስትመንት ፡ ግሩፕ ፡ የተገነባ ነው።
ሚድሮክ የሀገር ሀብት-ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ










