ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድንን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚድሮክ በወርቅ ምርት ሥራ ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ከፍ ያለ አስተዋጽዖ አበርክቷል ብለዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሻኪሶ


በሻኪሶ ከተማ የሚገኘዉንና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ አካል የሆነው ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተጎብኝቷል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የዕድሎች ማሳያ የሆነችና በአህጉሩም በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት አንዷ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል።

በወርቅ ክምችት የታደሉት የሻኪሶ እና ሰፊው የጉጂ አካባቢ የማዕድን ማውጣት ሥራው ዐቢይ ስፍራዎች ናቸው ሲሉም ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሻኪሶ በነበራቸው ጉብኝት በኢትዮዽያ መሪ የወርቅ ምርት ኩባንያዎች አንዱ የሆነውን የሚድሮክ ወርቅ የሥራ እንቅስቃሴንም ተመልክተዋል።

ተቋሙ በዘርፉ ቀዳሚ እንደመሆኑ በትልቅ አቅም እና ደረጃ በሚሰራው የወርቅ ምርት ሥራ ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ከፍ ያለ አስተዋጽዖ አበርክቷል ብለዋል።

በጉብኝቱ ላይ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ እና የማዕድን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዱላ መኮንን፣ የግብርና ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ታደሰ፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አካለወልድ አድማሱን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ABOUT MIDROC INVESTMENT GROUP

MIDROC Investment Group is a group of Sheikh Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi’s companies, mainly engaged in Agriculture, agro-processing, Manufacturing, Mining, Construction, Real-estate, Hotel, Tourism and Commercial endeavors.

READ MORE

OUR LEADERSHIP

Our senior executives bring tremendous experience, visionary thinking and a shared commitment to excellence, creativity, and innovation to the future as well as  the day to day operation of the company.

READ MORE

  • RMOHA SOFT Drinks Industry
  • AMANUFACTURING CLUSTER QUALITY POLICY