ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ
በወርቅ ደረጃ ተሸላሚ የሆኑት 10 ድርጅቶች ሲሆኑ እነርሱም፡-




- ሚድሮክ ወርቅ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ሆራይዘን አዲስ ጎማ ኃ.የተ.የግ.ማ
- አህፋ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማ.
- የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ኮንቦልቻ የብረታብረት ማምረቻ ኢንደስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. (ኮስፒ)
- ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ.የተ.የግ.ማ ሲሆኑ
በብር ደረጃ የተሸለሙት 8 ድርጅቶች ደግሞ፡- - ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- አዲስ ጋዝ እና ፕላስቲክ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ዘመናዊ የህንፃ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. (ኤም.ቢ.አይ)
- ብሉናይል የፖሊፕሮፕሊንና ክራፍት ከረጢት ማምረቻ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ሰሚት ኢንጂነርድ ፕላስቲክ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- አንሊሚትድ ፓኬጂንግ ኃ.የተ.የግ.ማ.
- ሁዳ ሪል እስቴት ኃ.የተ.የግ.ማ. እና
- ኩዊንስ ሱፐርማርኬቶች ኃ.የተ.የግ.ማህበር ናቸው፡፡
ሽልማቱንም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ እና የየድርጅቶቹ ዋና ሥራ አስኪያጆች ከክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅ ተቀብለዋል፡፡
ሥራ አስኪያጆቹ ሽልማቱን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ለቀጣይ ዓመት ከዚህ ለተሻለ ዉጤት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
እንደ ሃላፊዎቹ ገለፃ ይህ ዉጤት የተገኘው በሁሉም ድርጅቶች ስር ያሉ ሰራተኞች ጠንክረው በመስራታቸው ነው፡፡
በቀጣይም ሰራተኞቹ በባለቤትነት ስሜት መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2012 ዓ.ም መጨረሻ እንደ አዲስ ከመዋቀሩና የአመራር ለውጥ ከማድረጉ በፊት በስሩ የሚገኙ በርካታ ድርጅቶቹ ኪሳራ ውስጥ የነበሩና ለሠራተኞቻቸው ደሞዝ ለመክፈልም ጭምር ይቸገሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡
በ2014 ዓ.ም የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ሽልማት ላይ 12 የተቋማችን አባል ድርጅቶች በወርቅና በብር ደረጃ መሸለማቸው ይታወሳል።